ስለችግኝ
ችግኝ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የሥራ ፈጣሪነትን ከፍ ለማድረግ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ኢንቬስትመንት ለማድረግ የተዘጋጀ የቴሌቪዥን ትርዒት ነው፡፡ ለሥራ ፈጣሪዎች የካፒታል እና የአስተዳደር ችሎታን የሚያገኙበት መድረክ ሲሆን ትርኢቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ ፈጣሪዎችን ፣ ወጣቶችን እና በአጠቃላይ ህብረተሰቡን ስለሥራ ፈጣሪነት ፣ ስለግል ምዋእለ ነዋይ አስተዳደር ፣ ስለኢንቬስትመንትና ስለግል ዘርፍ ለማበረታታት እና ለማስተማር የተዘጋጀ ፕሮግራም ነው፡፡
ሥራ ፈጣሪዎች ለመወዳደር ካመለከቱ በኋላ በግል ምዋእለ ነዋይ አስተዳደር ላይ እና የንግድ ሥራዎቻቸውን ለማስፋት በሚረዱ ምርጥ ልምዶች ላይ ሥልጠና ያገኛሉ፡፡ ለዝግጅቱ የተመረጡት ሥራ ፈጣሪዎች በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ለባለሀብቶች ፓነል አቅርበው ግብረመልስ እና ስልጠና ይቀበላሉ፡፡ በጣም ጥሩ የንግድ ሥራ ኖሮዋቸው የተገኙ ሥራ ፈጣሪዎች ኢንቬስትሜቶችን ያገኛሉ፡፡ እርስዎ ሥራ ፈጣሪ ነዎት? የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ ለመቅረብ ይመዝገቡ::